የዋልያዎቹ ጨዋታ የቴሌቪዥን ሽፋን ያገኛል

ዋልያዎቹ በቻን ማጣርያ በትግራይ ስታዲየም የሚያደርጉትን ጨዋታ በትግራይ መገናኛ ብዙሃን (ኤመሐት) በትግራይ ቴሌቪዥን በኩል የቀጥታ ሽፋን ያገኛል።

የቴሌቭዥን ጣቢያው ከዚ ቀደም በርካታ ጨዋታዎች በቀጥታ ያስተላለፈ ሲሆን አሁን ደግሞ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በመቐለ የሚደረገውን የብሔራዊ ቡድን ጨዋታ በቀጥታ እንደሚያስተላልፍ አስቀድሞ ገልጿል።

በሌላ ዜና ቀጣይ እሁድ ኢትዮጵያን የምትገጥመው ሩዋንዳ በአቋም መለኪያ ጨዋታ ወደ ኪንሻሳ አምርታ ኮንጎን 2-3 አሸንፋለች።


© ሶከር ኢትዮጵያ