ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የቻን ማጣርያ ጨዋታን ይመራሉ

የቻን ማጣርያ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ሲከናወኑ ታንዛንያ ላይ የሚደረገው ጨዋታ በኢትዮጵያውያን ዳኞች ይመራል።

ታንዛንያ ላይ እሁድ ምሽት ታንዛንያ ከ ሱዳን የሚያደርጉትን ይህን ጨዋታ በላይ ታደሰ በዋና ዳኝነት ሲመራው በረዳት ዳኝነት ክንፈ ይልማ እና ትግል ግዛው አብረውት ይመራሉ። አራተኛ ዳኛ ደግሞ ቴዎድሮስ ምትኩ እንዲሆን በካፍ ተመድቧል።

በላይ ታደሰ እና ረዳቶቹ ባለፈው ሳምንት በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የዩጋንዳው ኬሲሲኤ ከአንጎላው ፔትሮ ዲ ሎዋንዳ ያደረጉትን ጨዋታ መምራታቸው የሚታወስ ነው ።


© ሶከር ኢትዮጵያ