ቻን 2020 | ሩዋንዳዎች መቐለ ገብተዋል

ካሜሩን ለምታዘጋጀው የ2020 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በቀጣይ እሁድ ኢትዮጵያን የሚገጥመው የሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድን ልዑካን ቡድን ዛሬ ጥዋት መቐለ ራስ አሉላ አባነጋ የአየር ማረፍያ ደርሰዋል።

ከቀናት በፊት በአቋም መለኪያ ጨዋታ ወደ ኮንጎ ኪንሻሳ ተጉዘው ኮንጎን 2-3 ያሸነፉት አማቩቢዎቹ 26 ተጫዋቾች ያካተተ ልዑካን ቡድን በመያዝ ነው መቐለ የገባው። በቪንሰንት ሚሻሚ የሚመሩት ሩዋንዳዎች በመጨረሻው የነጥብ ጨዋታ በዓለም ዋንጫ ማጣርያ በኪጋሊ ሲሸልስን ገጥመው ሰባት ለባዶ ማሸነፋቸው ይታወሳል።

በሌላ ዜና አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱና የቡድኑ አምበል አስቻለው ታመነ ከሩዋንዳ አቻዎቻቸው ጋር ነገ 11 ሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ