ኢትዮጵያ ቡና | የካሳዬ አራጌ ረዳት አሰልጣኝ ታውቋል

ኢትዮጵያ ቡና የካሳዬ አራጌ ቅጥር ከፈፀመ በኋላ ምክትሉን ሳያሳውቅ ቢቆይም በመጨረሻም ዘላለም ፀጋዬን ቀጥሯል።

አሰልጣኝ ዘላለም በተጫዋችነት ዘመኑ ለአየር መንገድ፣ ወንጂ ስኳር፣ ኢትዮጽያ ቡና እና ኢትዮጵያ መድን እንዲሁም የየመኑ ኤ ሪሽን ማርዮ የተጫወተ ሲሆን በአሰልጣኝነት ደግሞ በተስፋ ለኢትዮጽያ፣ ዋዜማ፣ ደደቢት ከ17 ዓመት በታች ሰርቷል።

አሰልጣኙ ካሳዬ አራጌ ለኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝነት ከተስማማ በኋላ ወደ ሀገር ውስጥ እስኪገባ ድረስ ተጫዋቾችን የመመልመል ሥራ ሲከውን መቆየቱ ሲነገር እንደነበር ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ