ሰበር ዜና | የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ጋዜጣዊ መግለጫ ሳይካሄድ ቀረ

ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በዛሬው ዕለት በሸራተን ሆቴል በወቅታዊ ጉዳይ በጋራ በመሆን ያዘጋጁት ጋዜጣዊ መግለጫ ሳይካሄድ ቀረ።

ከሰሞኑን ፌዴሬሽኑ አዳዲስ ይዟቸው የመጣቸው የሊግ አደረጃጀት፣ የሊግ ኩባንያ ምስረታ እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን አስመልክቶ በተዘጋጀው በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ክለቦቹ ፌዴሬሽኑ እየሄደባቸው ባሉ አካሄዶች ዙርያ ያላቸውን አቋም ለሚዲያው ይፋ የሚያደርጉ መሆናቸውን እና በአንድ ባለሙያ ጥናታዊ ፁሁፍ ለማቅረብ ጋዜጣዊ መግለጫ መጥራታቸው ይታወቃል።

ሆኖም በቦታው አቶ አብነት ገብረ መስቀል የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ሰብሳቢ፣ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የኢትዮጵያ ቡና ሰብሳቢ እና አቶ ኃይለየሱስ ፍስሀ (ኢንጅነር) እና ጥሪ የተደረገላቸው የሚዲያ አካላት በቦታው ተገኝተው የነበረ ቢሆንም መንግስት ትዕግስት አድርጉ ብሎ በመጠየቁ እንደሆነ ከመድረኩ ተነግሯል።

* ያሉትን አዳዲስ ነገሮች ወደ ኃላ በዝርዝር ይዘን የምንቀርብ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ