ቻን 2020| ዋልያዎቹ ለነገው ጨዋታ የመጨረሻ ልምምዳቸውን አከናወኑ

በቻን ማጣርያ በነገው ዕለት ሩዋንዳን የሚገጥሙት ዋልያዎቹ ዛሬ ጠዋት ልምምዳቸውን በተሳካ ሁኔታ ሲያከናውኑ ቀላል ጉዳት ገጥሟቸው የነበሩ ተጫዋቾችም ልምምድ ሰርተዋል።

ዛሬ ጠዋት በትግራይ ስታድየም ባደረጉት የመጨረሻ ልምምዳቸው ከቀናት በፊት ቀላል ጉዳት ገጥሟቸው የነበሩት ጀማል ጣሰው እና ከነዓን ማርክነህ ልምምድ ሰርተዋል። ከነዓን ማርክነህ ዛሬ ከቡድኑ ጋር ተቀላቅሎ ልምምድ ሲሰራ ግብጠባቂው ጀማል ጣሰው ግን በግሉ ቀላል ልምምድ ሲሰራ እንደመስተዋሉ ለነገው ጨዋታ መድረሱ አጠራጣሪ ነው።

ነገ 10:00 በትግራይ ስታዲየም ሩዋንዳን የሚገጥሙት ዋልያዎቹ ከ27 ቀናት በኃላ (ኦክቶበር 19) በኪጋሊ ስቴድየም የሁለተኛውን ጨዋታ የሚያካሂዱ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ