አርባምንጭ ከተማ የሦስት ተጫዋቾች ዝውውር አጠናቀቀ

በአዲሱ ፎርማት መሰረት ፕሪምየር ሊጉን በድጋሚ የተቀላቀለው አርባምንጭ ከተማ ተጫዋቾችን ማስፈረም ጀምሯል።

በዘንድሮ ውድድር ዓመት በነቀምቴ ከተማ ስኬታማ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ዳንኤል ዳዊት ወደ አርባምንጭ አምርቷል። ዳንኤል የእግር ኳስ ህይወቱን በነቀምቴ ጀምሮ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የቆየ ሲሆን በ2011 በከፍተኛ ሊጉ ለኮከብ ግብ አግቢነት ሲፎካከር ነበር።

ሌላው ወደ አርባምንጭ ያመራው ገመችስ ማኑኤ በነቀምቴ በቀኝ ተከላካይነት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ ወደ አዞቹ ያመራ ሁለተኛ ተጫዋች ሆኗል። ገመችስ በኢትዮጽያ ንግድ ባንክም ከዚህ ቀደም ተጫውቷል።

የአዞቹ ሦስተኛ ተጫዋች ሆኖ ቡድኑን የተቀላቀለው አብነት ተሾመ ነው። የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው አብነት በሀላባ እና በሀምበሪቾ መጫወት ችሏል።

አርባምንጭ በቅርቡ ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቹችን ወደ ቡድኑ እንደሚቀላቅል ያሳወቀ ሲሆን የሰባት ተጫዋቾችንም ውል አድሷል። ይታገሱ አበበ፣ ጆንቴ መንግስቱ፣ አሸናፊ ተገኝ፣ መስቀሉ ለቴቦ፣ ዳግም ዓለማየሁ፣ ቡታቃ ሻመና እና አሸናፊ ያደሱ ተጫዋቾች ናቸው።


© ሶከር ኢትዮጵያ