አፈወርቅ ኃይሉ ለሀዲያ ሆሳዕና ፊርማውን አኑሯል

ለባህር ዳር ከተማ ለመጫወት ተስማምቶ የነበረው አፈወርቅ ኃይሉ ለሀዲያ ሆሳዕና ፊርማውን አኑሯል።

ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከወልዋሎ ዓ.ዩኒቨርስቲ ጋር ጥሩ ቆይታ ያደረገው አፈወርቅ ከሳምንታት በፊት ለባህር ዳር ከተማ ለመጫወት መስማማቱን ክለቡን (ባህር ዳር ከተማ) ዋቢ አድርገን መዘገባችን ይታወሳል። ይሁንና የተጨዋቹ ፊርማ በፌደሬሽኑ የፀና ባለመሆኑ ተጨዋቹ የተሻለ ውል ወዳቀረበለት ሀዲያ ሆሳዕና ማምራቱ ታውቋል። በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ጥሪ ቀርቦለት መጫወት የቻለው ተጨዋቹ ለአንድ ዓመት በሀዲያ ሆሳህና ቤት ለመቆየት መስማማቱ ታውቋል።

በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሚመሩት ሀዲያ ሆሳናዎች ከዚህ ቀደም ይሁን እንዳሻው፣ ሄኖክ አርፊጮ፣ ደስታ ጊቻሞ፣ አብዱሰመድ ዓሊ፣ ሱራፌል ዳንኤል፣ በረከት ወልደዮሀንስ እና መስቀሉ ለቴቦን ወደ ቡድናቸው ሲቀላቅሉ ለማስፈረም ተስማምቶ የነበረው ብሩክ ኤልያስ በደቡብ ፖሊስ ቀሪ ውል ያለው በመሆኑ ወደ ክለቡ መመለሱ ተሰምቷል።።


© ሶከር ኢትዮጵያ