እሸቱ መና ደቡብ ፖሊስን ተቀላቀለ

የቀኝ መስመር ተከላካዩ እሸቱ መና ለደቡብ ፖሊስ ፊርማውን አኑሯል።

ወደ ቀድሞ ክለቡ ደቡብ ፖሊስ ከረጅም ጊዜ በኃላ የተመለሰው የቀኝ መስመር ተከላካዩ በወላይታ ድቻ በሁለት አጋጣሚዎች ተመልሶ መጫወት የቻለ ሲሆን በአዳማ ከተማ ቆይታን ካደረገ በኋላ ባለፉት ሁለት ዓመታት በድጋሚ ተመልሶ በወላይታ ድቻ ተጫውቶ አዲሱን የአሰልጣኝ ተመስገን ዳና ቡድንን ዛሬ መቀላቀሉ ታውቋል፡፡

በቀጣዮቹ ቀናትም ተጨማሪ ተጫዋቾችን እንደሚጨምሩ የሚጠበቁት ቢጫ ለባሾቹ ክለቡን ለማጠናከር ከወጣት ተጫዋቾች ባለፈ ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች በመቀላቀል ላይ እንደሆኑ አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ