የከፍተኛ ሊጉ ግብ አስቆጣሪ ወደ ባህርዳር ለማምራት ተስማማ

ከአርባምንጭ ከተማ ጋር የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገውና ወደ አዳማ ለማምራት ተስማምቶ የነበረው ስንታየው መንግስቱ ወደ ጣና ሞገደኞቹ ቤት ለማቅናት ከስምምነት ደርሷል፡፡

ከወላይታ ድቻ ካደገ በኃላ በክለቡ ዋናው ቡድን መጫወት የቻለው ይህ ወጣት የፊት መስመር ተሰላፊ ድቻን ከለቀቀ በኃላ በ2010 ወደ ሀላባ ከተማ አምርቶ የክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን መጨረስ የቻለ ሲሆን ወደ ቀድሞ አሰልጣኙ መሳይ ተፈሪው አርባምንጭ ከተማ አምርቶ በ2011 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ኮከብ ግብ አግቢ በመሆን በ15 ግቦች ማጠናቀቁ ይታወሳል። በቅርቡም ወደ አዳማ ከተማ ተጉዞ ለመጫወት ከስምምነት የደረሰ ቢሆንም ከክፍያ ጋር በተያያዘ ከክለቡ ጋር ሳይስማማ በመቅረቱ ዛሬ የባህርዳር ከተማ አዲስ ፈራሚ ለመሆን መስማማት ችሏል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ