አዳማ ከተማ የቀድሞ ተጫዋቹን ወደ ቡድኑ መልሷል

በአዳማ ከ17–20 ዓመት በታች ቡድን መጫወት የቻለውና በኢትዮጵያ ቡና የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገው የኋላሸት ፍቃዱ ወደ አሳዳጊ ቡድኑ ተመልሷል።

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የረጅም ዓመት ኮንትራት ቢፈርምም አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ የተወሰኑ ተጫዋቾችን በቡድኑ ለማቆየት የሙከራ ጊዜ መስጠት አለብኝ በማለቱ ቅሬታቸውን ካሰሙ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው አጥቂው የኃላሸት ፍቃዱ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በስምምነት ከተለያየ በኃላ ማረፊያውን ወደ አሳዳጊ ክለቡ አዳማ ከተማ አድርጓል።

በአዳማ ከ17–20 ዓመት በታች ቡድን ታዳጊ ቡድን በተደጋጋሚ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ባጠናቀቀባቸው ዓመታት ወደ ዋናው ቡድን ያድጋል ተብሎ ቢጠበቅም ይህ አለመሆኑ ተከትሎ በገላን ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና መጫወት ችሎ ነበር።


© ሶከር ኢትዮጵያ