ሴካፋ ከ20 ዓመት በታች| ኢትዮጵያ ከምድብ ስትሰናበት ታንዛንኒያ በሰፊ ውጤት አሸንፋለች

* የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች እሁድ ይደረጋሉ

ከአንድ ሳምንት በፊት የተጀመረው እና በሰፊ ውጤት በተጠናቀቁ ጨዋታዎች ዛሬ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ያስተናገደው የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ወደ ሩብ ፍፃሜ ያለፉ ሀገራትን ለይቷል።

ጠባብ የማለፍ ዕድል በመያዝ ወደ ጨዋታው ያመራችው ሃገራችን ኢትዮጵያ በኬንያ 4-0 ተሸንፋ ካለ ምንም ነጥብ ከውድድሩ ውጭ ሆናለች። የኬንያ የማሸነፍያ ግቦችም በስቲቭ ኦቲኖ ፣ ኦስቲን ኦዲሃምቦ ፣ ጆን ጅጉና እና ቤንሶም ኦማላ አማካኝነት የተገኙ ናቸው።

ሁለተኛ ጨዋታ የነበረው የዛንዚባር እና የታንዛንያ ፍልሚያ በታንዛንያ 5-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች እሁድ መደረግ ሲጀምሩ ተጋጣሚዎቹም ተለይተው ታውቀዋል፡-

(ፉፋ ቴክኒካል ሴንተር )
ብሩንዲ ከ ኬንያ ( 7 ሰዓት)
ኤርትራ ከ ዛንዚባር ( 10 ሰዓት)

(ፒስ ስቴድየም)
ሱዳን ከ ደቡብ ሱዳን ( 7 ሰዓት)
ዩጋንዳ ከ ታንዛንያ ( 10 ሰዓት)


© ሶከር ኢትዮጵያ