ባህር ዳር ከተማ ማሊያዊውን አጥቂ ለማስፈረም ተስማማ

በጅማ አባጅፋር ጥሩ ቆይታ የነበረው ማሊያዊው አጥቂ ማማዱ ሲዲቤ ባህር ዳር ከተማን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል፡፡

የ26 ዓመቱ አጥቂ በ2011 የውድድር ዘመን የሞሮኮውን ራፒድ ኦውድን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በጅማ አባጅፋር በግሉ የተሳካ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን በፕሪምየር ሊጉ እና በአፍሪካ ውድድር ጥሩ እንቅስቃሴ ከማሳየቱ በተጨማሪ ወሳኝ ጎሎችንም ማስቆጠር ችሏል።

በርካታ ተጫዋቾችን ያስፈረሙት የጣና ሞገዶቹ ከቀድሞው ኦሊምፒክ ኮሪብጋ፣ ራቻድ ቤርኖውሲ እና ኤኤስ ፖሊስ አጥቂ በተጨማሪ ከቀናት በፊት የከፍተኛ ሉጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የሆነውን አጥቂ ስንታየው መንግስቱን ማስፈረማቸውም ይታወሳል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ