ባህር ዳር ከተማ የግብ ጠባቂውን ውል አራዝሟል

ከሰዓታት በፊት ተጨማሪ ተጨዋች ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል የተስማሙት የጣና ሞገዶቹ የግብ ጠባቂያቸውን ውል አራዝመዋል።

የ25 ዓመቱ ቤኒናዊ ግብ ጠባቂ ሃሪስተን ሄሱ ከጣናው ሞገዶቹ ጋር ለመቆየት ውሉን ለአንድ ዓመት አራዝሟል። ዓምና ከኢትዮጵያ ቡና ወደ ባህር ዳር ከተማ በመዘዋወር የ2010 የውድድር አመትን በኢትዮጵያ ያሳለፈው ተጨዋቹ በውድድር ዓመት ጅማሮ ላይ በቋሚነት መሰለፍ ሳይችል መቅረቱ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ቀስ በቀስ የቋሚነት ቦታን ከምንተስኖት አሎ እየወሰደ ጥሩ ግልጋሎት አበርክቷል።

በ2008 ኤ ኤስ ድራጎንስን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ያመራው ተጨዋቹ ለሁለት ዓመታት በቡናማዎቹ ቤት ቆይቶ ዓምና ወደ ባህርዳር ማቅናቱ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ