ስሑል ሽረ የአሰልጣኙን ውል አራዝሟል

የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ከሁለተኛው ዙር ጀምሮ በአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ እየተመራ በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠው ስሑል ሽረ የአሰልጣኙን ውል አራዝሟል፡፡

ለአንድ ዓመት ያህል ከአሰልጣኝነት ከራቁ በኋላ ነበር ወደ አሰልጣኝነት በመመለስ ስሑል ሽረን መያዝ የቻሉት የቀድሞ የዳሽን ቢራ እና ሐረር ሲቲ አሰልጣኝ ሽረን በውድድር ዓመቱ አጋማሽ ከተረከቡ በኋላ ቡድኑ ውጤቱ እንዲሻሻል ያደረጉ ሲሆን ይህን የተመለከተው ክለቡም ለተጨማሪ ዓመት በክለቡ ቆይታን ማድረግ እንዲችሉ ውላቸውን አድሷል፡፡

ክለቡ ከዋናው አሰልጣኝ በተጨማሪ መብራህቶም ፍስሀ በረዳትነት በአሰልጣኝ ቡድኑ ውስጥ ለተጨማሪ ዓመት እንደሚቆዩ አሳውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ