ከፍተኛ ሊግ | ገላን ከተማ አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

በአሰልጣኝ ዳዊት ታደሰ እየተመራ ባለፈው ዓመት ለመጀመርያ ጊዜ በተሳተፈበት የከፍተኛ ሊግ ውድድር ጥሩ ጉዞ ማድረግ የቻለው ገላን ከተማ ስድስት ተጫዋቾች ማስፈረም ችሏል።

በተከላካይ አማካይ ስፍራ ላይ የሚጫወቱት ዘሪሁን ዐቢይ (ከቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ)፣ ዳዊት ተፈራ (የካ ክፍለ ከተማ)፣ አማካዩ ኤርምያስ ኃይሉ (ከኢኮስኮ)፣ የተከለካዩ ስፍራ ተጫዋቹ ታሪክ እሸቴ (ከቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ)፣ አጥቂው ተመስገን ተስፋዬ (ከወሎ ኮምቦልቻ) እንዲሁም በኢኮስኮ ቆይታው የቡድኑ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የነበረው አበበ ታደሰ ለክለቡ የፈረሙ አዳዲስ ተጫዋቾች ናቸው።

በተያያዘ ቡድኑ የነባሮቹ ሚኪያስ አለማየው ፤ አንተነህ መሰለ እና ፍጹም ክፍሌን ውል ሲያድስ በቅርቡ ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾች ቡድኑን እንደሚቀላቅሉ ክለቡ ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ