ሚካኤል ጆርጅ ወደ ቀድሞው ክለቡ ተመልሷል

የፊት መስመር ተጫዋቹ ሚካኤል ጆርጅ የቀድሞ ክለቡ አዳማ ከተማን ዛሬ በይፋ ተቀላቅሏል፡፡

በሙገር ሲሚንቶ የተሳኩ ጊዜያትን ካሳለፈ በኋላ ወደ ሲዳማ ቡና አምርቶ መጫወት የቻለው የፊት አጥቂው ሚካኤል ሲዳማን ከለቀቀ በኋላ በደደቢት፣ ዳሽን ቢራ እና አዳማ ከተማ ተጫውቶ አሳልፏል። በከፍተኛ ሊጉ አውስኮድ አምርቶ የአንድ ዓመት ቆይታን ካደረገ በኋላም በድጋሚ ወደ ቀድሞ ክለቡ አዳማ ከተማ የመለሰውን ዝውውር በመፈፀም ክለቡን ተቀላቅሏል፡፡

በክረምቱ አጥቂዎችን ለማስፈረም ተስማምቶ ወደ ሌሎች ክለቦች ያመሩበት አዳማ ከተማ ከሚካኤል ጆርጅ በተጨማሪ በአጥቂ ስፍራ ላይ ኢትዮጵያ ቡናን የለቀቀውና ከዚህ ቀደም በክለቡ ወጣት ቡድን የተጫወተው የኋላሸት ፍቃዱን ወደ ቡድኑ መመለሱ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ