ኢትዮጵያ ቡና ከአማካይ ተጫዋቹ ጋር ሊለያይ ነው

ከወልዲያ ኢትዮጵያ ቡና በተቀላቀለበት ዓመት የመጀመርያ ተሰላፊ በመሆን ያገለገለው ዳንኤል ደምሴ ከቡናማዎቹ ጋር ለመለያየት ተቃርቧል።

ኢትዮጵያ ቡና የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በባቱ ከተማ እያደረገ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት ከቡድኑ ጋር አብሮ እየሰራ የማይገኘው ዳንኤል ደምሴ ምንም እንኳን ከክለቡ ጋር የሚያቆየው ቀሪ ኮንትራት ቢኖረውም ለመለያየት እየተደራደረ መሆኑን ሰምተናል።

በመጣበት ዓመት በተለያ በአዲስ አበባ ዋንጫ ላይ መልካም እንቅስቃሴ በማድረግ በፍጥነት በኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ልብ የገባው ዳንኤል በኃላም በተለያዩ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ለቡናማዎቹ ማገልገሉ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ