አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የሚጀመርበት ቀን ታውቋል

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የሚጀመርበት ጊዜ እና ተሳታፊ ክለቦች ታውቀዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የእግርኳስ ፌዴሬሽን አስተናጋጅነት የሚካሄደው ይህ ውድድር ከጥቅምት 22 ጀምሮ እስከ ህዳር 7 ሲካሄድ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መከላከያ፣ ኤሌክትሪክ ወልቂጤ እና ሰበታ ከተማ በውድድሩ መሳተፋቸው ተረጋግጧል። የኢኮስኮ እና የኢትዮጵያ መድን መሳተፍ ደግሞ አጠራጣሪ ሆኗል።

በውድድሩ የመሳተፋቸው ነገር አጠራጣሪ በሆኑት ሁለቱ ክለቦች ምትክም ሲዳማ ቡና እና ያለፈው ዓመት የውድድሩ ክስተት ባህርዳር ከተማ ሊሳተፉ እንደሚችሉ ተሰምቷል።

ከዓመት ዓመት በርካታ መሻሻሎች እያደረገ የሚገኘው ውድድሩ በዚህ ዓመት ውድድርም ከሽልማት ጀምሮ በርካታ ማሻሻያ አድርጎ እንደሚመለስ ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ