የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚጀምርበት ቀን ማስተካከያ ተደረገበት

የፕሪምየር ሊጉ ዐቢይ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው የመጀመርያው ስብሰባ የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከኀዳር 6 እና 7 ቀን እንደሚጀምር በመግለፁን ከደቂቃዎች በፊት መዘገባችን ይታወቃል።

ሆኖም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ኅዳር 6 ቀን ከሜዳ ውጭ ከማዳጋስካር፣ ኅዳር 9 ከአይቮሪኮስት ጋር ጨዋታ መኖሩን ከውሳኔው በኋላ በማረጋገጡ የቀን ለውጥ ማድረጉ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሠረት ኮሚቴው አንድ ሳምንት ወደፊት በመግፋት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2012 ውድድር ዘመን ኅዳር 13 እና 14 ቀን እንዲጀምር ማሻሽያ አድርጓል።

ዝርዝር የስብሰባዉን ውሎ ከቆይታ በኃላ እንመለስበታለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ