አዳማ ከተማ አጥቂ አስፈረመ

አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም እና የነባሮችን ውል በማራዘም ላይ የሚገኙት አዳማ ከተማዎች አጥቂው በላይ ዓባይነህ አስፈርመዋል።

ድሬዳዋ ከተማ በአሰልጣኝ መሠረት ማኔ እየተመራ ወደ ፕሪምየር ሊግ ባደገበት የብሔራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ያጠናቀቀው ይህ ተጫዋች ወልዲያ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ባለፈው የውድድር ዓመት ቤንች ማጂ ቡና የተጫወተባቸው ክለቦች ሲሆኑ በመሐል እና የመስመር አጥቂነት መጫወት ይችላል።

በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመሩ ዝግጅታቸው በማድረግ ላይ የሚገኙት አዳማዎች ሁለት የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ከአንድ የባቱ እና ከአንድ የመተሐራ ቡድኖች ጋር አድርገው በሰፊ ውጤቶች ያሸነፉ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ቢሾፍቱ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2-0 አሸንፈዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ