ለጋዜጠኛ ምስጋናው ታደሰ የሚደረገው ድጋፍ ቀጥሏል

እግሩ ላይ ባጋጠመው ህመም ህክምናውን እየተከታተለ የሚገኘው ጋዜጠኛ ምስጋናው ታደሰን ጤንነት ለመመለስ የሚደረገው ድጋፍ የቀጠለ ሲሆን የወልቂጤ ከተማ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ደጋፊ በግላቸው የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

የወልቂጤ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አበባው ሰለሞን የ10,000 ብር፤ የወልቂጤ ደጋፊ የሆነው ዮሐንስ ኃይሌ በስራኖ ኮንስትራክሽን ስም 20,000 ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ምስጋናውን መደገፍ የሚሻ አካል ወይም ግለሰብ በተጠቀሱት የባንክ አካውንቶች መጠቀም ይችላል

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – 1000268456639

አዋሽ ባንክ – 01320148371700


© ሶከር ኢትዮጵያ