ሀዲያ ሆሳዕና ጋናዊ አጥቂ ለማስፈረም ተስማማ

ጋናዊው አጥቂ ቢስማርክ ኒህይራ አፒያ ለሀዲያ ሆሳዕና ለመጫወት ስምምነት ላይ ደረሰ፡፡

የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ቢስማርክ ከዚህ ቀደም በሰርቢያው ሶልጋ ፔትሮቫግ፣ በቦትስዋናው ጋብሮኒ ዮናይትድ፣ በድጋሚ ወደ ሰርቢያ በመመለስ ባካ ፖላንካ እንዲሁም ማልዶስት ሉቻኒ ከተጫወተ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ያለፈውን የውድድር ዓመት በጅማ አባጅፋር ግማሽ የውድድር ዓመት አሳልፏል። በመቀጠልም ሁለተኛውን የውድድር ዘመን አጋማሽ ወደ ስሑል ሽረ አምርቶ መጫወት ችሏል፡፡

ቢስማርክ በቅርቡ ለክለቡ ከፈረመው ማሊያዊው ሙሳ ካማራ በመቀጠል በሆሳዕና ሁለተኛ አዲስ የውጪ ዜጋ ፈራሚ ሆኗል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ