ስሑል ሽረ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ

በደደቢት ውሉን አራዝሞ የነበረው መድኃኔ ብርሃኔ ከቡድኑ ጋር በስምምነት ተለያይቶ ወደ ስሑል ሽረ አምርቷል።

ከደደቢት ሁለተኛው ቡድን አድጎ በ2010 ሁለተኛ ዙር ከዋናው ቡድን ጋር መጫወት የጀመረው መድኃኔ ባለፈው የውድድር ዓመት በግሉ ጥሩ ዓመት አሳልፎ ከሳምንታት በፊት ከደደቢት ጋር ለመቀጠል ቢስማማም ቡድኑ በከፍተኛ ሊግ እንደሚሳተፍ ከተረጋገጠ በኃላ በስምምነት ተለያይቶ ወደ ስሑል ሽረ የሚያደርገውን ዝውውር አጠናቋል። በመስመር ተከላካይነት፣ በመስመር ተጫዋችነት እና በአጥቂ ቦታ መጫወት የሚችለው ሁለገቡ ተጫዋች በውድድር ዓመቱ ለቋሚ ተሰላፊነት ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል።

ቀደም ብለው የአሰልጣኝ ሳምሶን አየለን ውል በማራዘም አስር ተጫዋቾች ያስፈረሙት ስሑል ሽረዎች በቀጣይ ቀናት ወጣት ተጫዋቾች ወደ ዋናው ቡድን ያሳድጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ