ከፍተኛ ሊግ | ሻሸመኔ ከተማ የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥር ፈፅሟል

አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ የሻሸመኔ አዲሱ አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።

አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም በባቱ ከተማ፣ ነገሌ ቦረና ፣ ሰበታ ከተማ ያሰለጠኑ ሲሆን ያለፉትን ዓመታት ደግሞ በቡራዩ ከተማ ሲሰሩ ቆይተዋል። አሰልጣኙ በተለይ በ2010 ቡራዩ ከተማ ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ እስከመጨረሻ እንዲፎካከር ማድረግ ችለዋል።

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ ዐምና ለጥቂት ከመውረድ የተረፉት ሻሸመኔዎች ዘንድሮ ይበልጥ ተጠናክሮ ለመቅረብ እየተንቀሳቀሱ ሲሆን ባቱ ከተማ ላይ ዝግጅታቸውን እያደጉ ይገኛሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ