ባህር ዳር ከተማ ማሊያዊውን ተከላካይ አስፈረመ

አዳዲስ ተጨዋቾችን በማስፈረም ቡድናቸውን እያጠናከሩ የሚገኙት ባህር ዳር ከተማዎች ዛሬ የተከላካይ መስመር ተጫዋች የሆነው አዳማ ሲሶኮን ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል።

ማሊያዊ ዜግነት ያለው ተጫዋቹ በ2010 ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከጅማ አባ ጅፋር ጋር ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ መሆን የቻለ ሲሆን በ2011 ደግሞ ቡድኑ በአህጉራዊ ውድድሮች ላይ ሲካፈል በአምበልነት ግልጋሎት መስጠቱ አይዘነጋም። ይህ በወጥነት ጥሩ ብቃት ሲያሳይ የነበረው ጠንካራ የተከላካይ መስመር ተጨዋች ወንድሜነህ ደረጄን ላጣው ቡድን ጥንካሬ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት የጣና ሞገዶቹ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በባህር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም እያከናወኑ ይገኛሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ