አንጋፋው አጥቂ ወደ ቀደሞ ክለቡ ተመልሷል

አንጋፋው አጥቂ ኤሪክ ሙራንዳ በ2010 ቆይታ ላደረገበት ደቡብ ፖሊስ ፈርሟል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ለረጅም ዓመታት መጫወት ከቻሉ የውጪ ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀሰው ኬኒያዊው አንጋፋ አጥቂ ኤሪክ ሙራንዳ በሀገሩ ኬኒያ እንዲሁም በዓለም ዙርያ ማልዲቭስ፣ ህንድ፣ ቬትናም፣ ሲንጋፖር፣ ማሌዥያ እና ኦማን ክለቦች ውስጥ መጫወት የቻለ ሲሆን በ1995 እና 96 በቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይታ ካደረገ በኋላ በድጋሚ በ2006 ተመልሶ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ ለሲዳማ ቡና የተጨመወተ ሲሆን በ2010 ደቡብ ፖሊስ፣ ባለፈው ዓመት ደግሞ ሀዲያ ሆሳዕና ጋር ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድጉ አስተዋፅኦ አበርክቷል። አጥቂው በተከታታይ ሦስት ዓመታት ወደ ፕሪምየር ሊግ በማደግ ታሪክ ለመስራት ወደ ደቡብ ፖሊስ ተመልሷል።

ኤሪክ ከጋናዊው አዳሙ መሐመድ፣ ከናይጄሪያዊው ላኪ ሰኒ እና ከዩጋንዳዊው ኢቫን ሳካዛ በመቀጠል አራተኛ የክለቡ ውጪ ዜጋ ተጫዋች ሆኗል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ