መቐለ 70 እንደርታ የግራ መስመር ተከላካይ አስፈረመ

ከመከላከያ ጋር የተለያየው አስናቀ ሞገስ ወደ መቐለ 70 እንደርታ አምርቷል።

በክረምቱ ቀደም ብሎ ለመከላከያ ፊርማው አኑሮ የነበረው ተጫዋቹ ጦሩ በፕሪምየር ሊጉ እንደማይሳተፍ በመረጋገጡ ከቡድኑ ጋር በስምምነት ተለያይቶ ነው ወደ ሊግ ቻምፒዮኖቹ መቐለዎች ያመራው።

ከዚ ቀደም በደደቢት፣ ኢትዮጵያ ቡናና በሁለት አጋጣሚዎች በባህር ዳር ከተማ መጫወት የቻለው ተጫዋቹ ባለፈው ዓመት የመጀመርያ ዙር ላይ ጠንካራ እና ጠጣር በነበረው እና ጥቂት ግቦች ያስተናገደው የባህርዳር ከተማ ተከላካይ ክፍል ቋሚ ተሰላፊ ሆኖ ነበር የውድድር ዓመቱን ያገባደደው።

ባለፈው የውድድር ዓመት ሄኖክ ኢሳይያስ፣ ያሬድ ሐሰን እና አንተነህ ገብረክርስቶስን በግራ መስመር ተከላካይነት አፈራርቀው የተጠቀሙት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በዚህ የውድድር ዓመት ኄኖክ ኢሳይያስን ወደ ተፈጥሯዊ የአማካይ ቦታው ይመልሱታል ተብሎ ሲጠበቅ አዲሱ ፈራሚ አስናቀ ሞገስ ከአንተነህ ጋር ለቦታው ይፎካከራል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ