ባህር ዳር ከተማ | የፋሲል ተካልኝ ረዳቶች ታውቀዋል

ከወራት በፊት የባህር ዳር ከተማ አሰልጣኝ ሆኖ የተሾመው ፋሲል ተካልኝ ምክትል እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኙ ታውቀዋል።

በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ለበርካታ ዓመታት በምክትል አሰልጣኝነት ያገለገለው ፋሲል ተካልኝ በባህር ዳር ከተማ በዋና አሰልጣኝነት ከተሾመ በኋላ ምክትሉን ሳያሳውቅ መቆቱ የሚታወስ ሲሆን ለቀናት ክለቡን ለብቻው (ከህክምና ክፍል ውጪ) የቅድመ ውድድር ዝግጅት በባህር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም ሲያሰራ ቆይቶ ረዳቶቹን ለክለቡ አመራሮች አሳውቋል።

በዚህም ታደሰ ጥላሁን የቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ ሆኖ ተመርጧል። አዲስ አበባ ከተማ እና ሱሉልታ ከተማን ጨምሮ በዋና እና በረዳት አሰልጣኝነት ለበርካታ ክለቦች ግልጋሎት የሰጠው ታደሰ ዛሬ በከተማው ተገኝቶ ከተጨዋቾች ጋር እንደተዋወቀ ተሰምቷል።

ከታደሰ በተጨማሪ አሻግሬ አድማሱ የቡድኑ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ተደርጎ እንደመረጠ ተረጋግጧል። አሻግሬ አድማሱ ከዚህ ቀደም በአሰልጣኝነት እና በተጨዋችነት በባህር ዳር ከተማ እና በባህር ዳር ጨርቃጨርቅ ማሳለፉ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ