የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት የሚካሄድበት ቀን ታወቀ

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት እና በውድድር ደንብ ዙርያ ውይይት የሚደረግበት ቀን ተለይቶ ታወቀ።

የዐቢይ ኮሚቴው ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ኮሚቴው ውድድሩን ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ የሠራቸውን ተግባራት በዝርዝር ከተናገሩ በኋላ የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት እና በውድድር ደንብ ዙርያ ውይይት የሚደረግበት ቀን ኅዳር 5 ቀን እንደሆነ ተናግረዋል። (ቦታ እና ሰዐት ወደፊት ይገለፃል)
የተሻሻለውን አዲሱን የውድድር መተዳደርያ ደንብ አስቀድመን ለክለቦቹ ቀደም እንዲላክ እደተደረገ እና መሻሻል ያለበት ሀሳብ አስተካክለው ይዘው በመምጣት ውይይት ከተደረገበት በኃላ ይፀድቃል። በዕለቱም የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ይገኛል ብለዋል።

ሊጉም ኀዳር 13 እና 14 ቀን እንደሚጀመር ገልፀዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ