የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ሥነ ስርዓት ኮሚቴ አባላት ተመረጡ

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚመራው ዐቢይ ኮሚቴ ውድድር ሥነ ስርዓት የኮሚቴን የሚመሩ ሰባት አባላትን ተመርጧል።

ወሎ ሠፈር በሚገኘው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዐቢይ ኮሚቴው ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ኮሚቴው ውድድሩን ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ የሠራቸውን ተግባራት በዝርዝር ተናግረዋል።

“የውድድር ሥነ ስርዓት ኮሚቴ በተመለከተ ከዚህ ቀደም ይሰራበት የነበረውን ከእኛ አስቀድሞ ፌዴሬሽኑ ማሻሻያ ለማድረግ አስቦ እንደነበር ቢታወቅም የውድድር እና ሥነ ስርዓት ኮሚቴ አስመልክቶ ለአባላቱ የሚሰጥ መመርያ አዘጋጅተናል። ሰባት የኮሚቴ አባላትን እንዲመረጡ አድርገናል። እንደ መስፈርት የተጠቀምነው የትምህርት ደረጃ ትንሹ የመጀመርያ ድግሪ ፣ እድሜ ከ60 ያልበለጠ ፣ ያለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በውድድር ታዛቢነት ፣ በኮሚሽነርነት ያልሠራ ይህ የተደረገበት ምክንያት ሁለቱን ዓመት በተለይ እግርኳሱ አስከፊ የሚባል ገፅታ አስተናግዶ አልፏል። የጅምላ ፍርድ በመፍረድ በዚህ ዙርያ የነበሩ ሰዎች እንዳይሳተፉ አድርገናል። በዚህም መሠረት ከላይ በቀረበው መስፈርት መሠተት ሰባታችን የዓብይ ኮሚቴ አባላት ይዘውት የመጡት እጩዎች ላይ ክርክር በማድረግ ሰባት ሰዎች ተመርጠዋል ” ብለዋል።

የተመረጡ ግለሰቦች

1 አቶ ሐብታሙ ኃይለሚካኤል
2 ዶ/ር ወገኔ ዋልተ ንጉስ
3 አቶ ወንድ አወቅ አበዜ
4 አቶ አብርሐም ተክላይማኖት
5 ኮማንደር ጌታቸው ኤጀርሶ
6 አቶ ዮናስ ገብረሚካኤል
7 አቶ ሞገስ በሪሁን

በእቅርቡ ኮሚቴዎቹ ተሰብስበው የራሳቸውን ሰብሳቢ እና ሌሎች የስራ ክፍፍል ያደርጋሉ ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት ስራቸውን እንዲሰሩ ይደረጋል።

ዝርዝር የጋዜጣዊ መግለጫውን ሐተታ ይዘን ከቆይታ በኃላ እንመለሳለን


© ሶከር ኢትዮጵያ