የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ በኢትዮጵያዊያን ዳኞች ይመራል

ዕሁድ ማፑቶ ላይ ዮዲ ሶንጎ እና ቢድቨስት ዊትስ የሚያደርጉትን የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ይመሩታል፡፡

በ2019/20 በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ሲሳተፉ ከቆዩ በኃላ ባስመዘገቡት ውጤት ወደ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የወረዱት የሞዛምቢኩ ክለብ ዮዲ ሶንጎ እና የደቡብ አፍሪካው ቢድቨስት ዊትስ የፊታችን ዕሁድ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ማፑቶ ላይ ያከናውናሉ፡፡ ልክ 10:00 ሲል በስታዲዮ ዶ ዚምፒቶ የሚደረገውን ይህን ጨዋታ አራት ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያዊያን ዳኞች እንዲመሩት ካፍ መምረጡን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችሁ መረጃ ይጠቁማል፡፡ በዋና ዳኝነት ቴዎድሮስ ምትኩ ሲመራ በረዳት ዳኝነት ተመስገን ሳሙኤል እና ኃይለራጉኤል ወልዳይ ያጫውታሉ፡፡ ብሩክ የማነብርሃን ደግሞ አራተኛ ዳኛ በመሆን በጋራ የሚያጫውቱ ይሆናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ