ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ አስፈርሟል

በዘንድሮ የውድድር ዘመን ተጠናክረው ለመምጣት እየሰሩ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ዛሬ ማሊያዊ ዜግነት ያለው አቱሳዬ ኒዮንዶን ወደ ስብስቡ መቀላቀሉ ታውቋል።

ይህ የ28 ዓመት አጥቂ ከ2007 ጀምሮ ለሃገሩ እና የደቡብ አፍሪካ ክለቦች መጫወት የቻለ ተጨዋች ነው። ለደቡብ አፍሪካዎቹ ብሎምፎንቴን ሴልቲክ፣ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ እና ፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲ የተጫወተው አጥቂው ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመምጣቱ ቀደም ብሎ ያለፉትን ስድስት ወራት በደቡብ አፍሪካ ናሽናል ዲቪዥን ክለብ ሻኩማ በመጫወት አሳልፏል።

ኒዮንዶ ከፓትሪክ ማታሲ፣ ኤድዊን ፍሪምፖንግ እና ዛቦ ቴጉዉይ በመቀጠል አራተኛው በፈረሰኞቹ ስብስብ ውስጥ የሚገኝ የውጪ ተጨዋች ሆኗል።


© ሶከር ኢትዮጵያ