የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ በኅዳር ወር ሊካሄድ ነው

ጥቅምት 1 ቀን ይካሄዳል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኅዳር ወር ሊካሄድ ይችላል።

መካሄድ ከነበረበት ጊዜ ዘግይቶ ጥቅምት 1 ቀን በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ አስቀድሞ ቢያሳውቅም በሀገር አቀፍ ደረጃ ጥቅምት ወር በሚካሄደው የስፖርት ምክር ቤት ጉባዔ ምክንያት የሚደረግበት ቀን ወደ ጥቅምት 29 ተገፍቶ ለማደረግ ታስቦ የነበረ ቢሆንም የሚለወጥ ነገር ከሌለ በቀር አሁን እየወጡ ባሉ መረጃዎች ኀዳር 6 ቀን ጠቅላላ ጉባዔውን ለማካሄድ መታሰቡን ሰምተናል።

ለወትሮም መነጋገርያ ጉዳዮች የማያጡት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ የተለመደው የ2010 ዕቅድ አፈፃፀም፣ የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥ መወያየት ማፅደቅ እና በተጓደሉ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ማሟላት እንዳለ ሆኖ ከወዲሁ ብዙ ክርክሮች ያስነሳል ተብለው የሚጠበቁ በርከት ያሉ አዳዲስ አጀንዳዎች በዕለቱ ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ