ወልዋሎ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ይሳተፋል

ቢጫ ለባሾቹ ከጥቅምት 22 ጀምሮ የሚካሄደው 14ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ እንደሚሳተፉ ታውቋል።

ባለፈው የውድድር ዓመት በትግራይ ክልል ዋንጫ ላይ ተሳታፊ የነበሩት ቢጫ ለባሾቹ በዚህ ዓመት ተመሳሳዩ ውድድር የመዘጋጀቱ ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ በመግባቱ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ለመሳተፍ ከውሳኔ ደርሰዋል።

በትናንትናው ዕለት ባህር ዳር ከተማ እንደሚሳተፍ የተረጋገጠበት ውድድሩ በቀጣይ ቀናትም ሌሎች ተጨማሪ ተጋባዥ ቡድኖችን ያሳውቃል ተብሎ ሲጠበቅ በመቐለ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በማድረግ ላይ የሚገኙት ወልዋሎዎች ከተለያዩ ክልሎች ተጋባዥ ክለቦችን በሚያሳትፈው በዚህ ውድድር ከትግራይ ክልል የሚሳተፉ የመጀመርያ ቡድን ይሆናሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ