አንተነህ ተስፋዬ ወደ ሰበታ ከተማ አምርቷል

ሰበታ ከተማ ወደ መከላከያ አምርቶ የነበረው የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ አንተነህ ተስፋዬን በእጁ አስገብቷል፡፡

ከወራት በፊት ለመከላከያ ለመጫወት ፈርሞ የነበረው ተጫዋቹ ቡድኑ በከፍተኛ ሊጉ እንዲጫወት በመወሰኑ ክለቡን በስምምነት ከለቀቀ በኋላ ነው ወደ ሰበታ ሊያመራ የቻለው። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ ተካቶ የሚገኘው የቀድሞው የአርባምንጭ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ተጫዋች አንተነህ በድሬዳዋ ከተማ ሁለት ድንቅ ዓመታትን ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የሚሳተፈው ሰበታ ከተማ በነገው ዕለትም ሁለት የውጪ ሀገር የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቾችን ሊያስፈርም እንደሚችል የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ዓለማየሁ ምንዳ ለሶከር ኢትዮጵያ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ