ሲዳማ ቡና ሀብታሙ ገዛኸኝን ዳግም አግኝቷል

ሲዳማ ቡናዎች ከወር በፊት ለመከላከያ ለመጫወት ተስማምቶ የነበረው የመስመር እና የፊት አጥቂው ሀብታሙ ገዛኸኝን በድጋሚ ማስፈረም ችለዋል፡፡

የቀድሞው የደቡብ ፖሊስ ተጫዋች ከ2010 እስከ ዐምና ድረስ በሲዳማ ቡና ሲጫወት የቆየ ሲሆን ውሉ በመጠናቀቁም በዛው በሲዳማ ቡና ይቀጥላል ሲባል የቆየ ቢሆንም ኋላ ላይ ወደ መከላከያ ማምራቱ ይታወሳል፡፡ መከላከያም በፕሪምየር ሊጉ መሳተፍ እንደማይችል በመታወቁ ጦሩን በመልቀቅ በድጋሚ የአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን ስብስብ ዛሬ ተቀላቅሏል፡፡

በተያያዘ የክለቡ ዜና ወደ ዱባይ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት እና በዛው በሚዘጋጅ ውድድር ላይ ተካፋይ ለመሆን በአንድ ግለሰብ አማካኝነት እንደሚጓዙ ተገልፆ የነበረ ቢሆንም ክለቡ ወደ ስፍራው እንደማያመራ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ