ከፍተኛ ሊግ | ገላን ከተማ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

በአሰልጣኝ ዳዊት ታደሰ እየተመራ ዝግጅቱን በአዳማ ከተማ እያደረገ ያለው ገላን ከተማ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾች ማስፈረም ችሏል።

ወንድማገኝ አብሬ ወደ ገለን ካመሩት መካከል ነው። የአጥቂ መስመር ተሰላፊው በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ጥሩ ጊዜያትን አሳልፎ ዐምና አጋማሹ ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ተቀላቅሎ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ተጫውቷል።

ግብ ጠባቂው ተመስገን ጮኖሬ ሌላው የገላን አዲስ ፈራሚ ነው። የቀድሞው የወልቂጤ ከተማ ግብ ጠባቂ ወደ ደቡብ ፖሊስ አምርቶ የነበረ ቢሆንም በስምምነት ተለያይቶ ወደ ቀድሞ ቡድኑ ገላን ከተማ አምርቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ