ስሑል ሽረ ከመከላከያ ጋር የተለያየውን ግብ ጠባቂ የግሉ አደረገ

ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆየው ምንተስኖት አሎ ማረፍያው ስሑል ሽረ ሆኗል።

ከዚ በፊት በሰበታ ከተማ፣ ፋሲል ከነማ እና ባህር ዳር ከተማ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ የጣና ሞገዶቹ ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲያድጉ የጎላ ድርሻ ነበረው። በዚህ ዓመት መጀመርያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ማልያ ለብሶ መጫወት የጀመረው ተጫዋቹ በኦሊምፒክ ማጣርያ እና በቻን ማጣርያዎች የአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ተቀዳሚ ተመራጭ መሆን ችሏል። በክረምቱ ወደ መከላከያ አምርቶ የነበረ ቢሆንም ክለቡ በከፍተኛ ሊግ እንዲሳተፍ በመወሰኑ ከቡድኑ ጋር መለያየቱም የሚታወስ ነው።

ፊቱን ወደ ሃገር ውስጥ ግብ ጠባቂ ለማዞር በመወሰን ፀ በረከት አማረ እና ሶፈንያስ ሰይፈን ለማስፈረም ጥረቶች አድርገው የነበሩት ስሑል ሽረዎች ምንተስኖት አሎን ማስፈረማቸው ተከትሎ በቀጣይ ዓመት በኢትዮጵያዊ ግብጠባቂ የጎል በራቸውን እንደሚያስጠብቁ ተረጋግጧል።
እንደሚታወሰው ቡድኑ ውሉ ከጨረሰው ናይጀርያዊ ግብ ጠባቂ ሰንደይ ሮትሚ በመለያየት ወንድወሰን አሸናፊ ከኢትዮጵያ ቡና አስፈርሞ የተክላይ በርኸን ውል አራዝሟል።


© ሶከር ኢትዮጵያ