የደቡብ ካስቴል ዋንጫ የቦታ እና የቀን ለውጥ ተደረገበት

ከጥቅምት 15 ጀምሮ በሀላባ ሊደረግ የነበረው የደቡብ ካስቴል ዋንጫ የቀን እና ቦታ ለውጥ ተደርጎበታል።

በደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚደረገውና በካስቴል ቢራ ስያሜ የተሰጠው የደቡብ ካስቴል የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ውድድር ከጥቅምት 15 ጀምሮ በሀላባ ከተማ ለማድረግ ታስቦ የነበረ ቢሆንም የሀላባ ከተማ ሜዳ በዕድሳት ላይ በመሆኑ ለውድድሩ እንደማይደርስ ታውቋል። በዚህም ውድድሩ በሀዋሳ ከተማ እንዲደረግ የተወሰነ መሆኑን አቶ ወልደሚካኤል መስቀሌ የፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኃላፊው ጨምረውም ውድድሩን በአምስት ቀን ወደፊት በመግፋት ጥቅምት 20 እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ