ስሑል ሽረ የሴቶች ቡድን ሊያቋቁም ነው

ስሑል ሽረ የሴት ቡድን ለማቋቋም መወሰኑን የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋይ ዓለም ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ 

እንደ ስራ-አስኪያጁ ገለፃ ከሆነ ቡድኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ላይ የማይካፈል ሲሆን ከዘንድሮው ዓመት ጀምሮ ተጫዋቾችን በመመልመል እና አሰልጣኝ በመቅጠር በዛው አካባቢ በሚዘጋጁ ውድድሮች ላይ እየተሳተፈ ይቆያል። ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት በዚሁ ቀጥሎ ቡድኑ በሚገባ መዋሀድ ከቻለ በኃላ በፌዴሬሽኑ ስር በሚዘጋጁ ውድድሮች ላይ ተካፋይ እንደሚሆንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ክለቡ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ተጫዋቾችን ወደ መመልመል ስራ የሚገባ ሲሆን በቅርቡ የሴት ቡድኑ ጨምሮ ከ15 እና 17 ዓመት በታች የወንዶች ቡድንን ለማቋቋም በማሰቡ የአሰልጣኞች ቅጥር ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ