ወልቂጤ ከተማ ከከፍተኛ ሊጉ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

ወልቂጤ ከተማ ዓባይነህ ፊኖ እና አቤኔዘር ኦቴን አስፈርሟል፡፡

ዓባይነህ ፊኖ ዐምና በከፍተኛ ሊጉ ኢኮስኮ ድንቅ የውድድር ጊዜ የነበረው ሲሆን የቀድሞው አሰልጣኝኙን ተከትሎ ወደ ወልቂጤ አምርቷል፡፡ ሌላኛው የግራ መስመር ተከላካዩ ወጣቱ አቤንኤዘር ኦቴ ከዚህ ቀደም በጂንካ ከተማ እና ደቡብ ፖሊስ የተጫወ ሲሆን ከአሰልጣኝ ደግአረግ ጋር ዐምና በኢኮስኮ አብሮ በመስራት ከቻለ በኋላ በወልቂጤም ዳግም ተገናኝተዋል፡፡

በተያያዘ የክለቡ ዜና ለክለቡ ለመጫወት ቀደም ብለው ተስማምተው የነበሩት ሶሆሆ ሜንሳህ፣ ጃኮ አራፋት እና ተከላካዩ ዐወል ከድር ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ