የጅማ አባጅፋር እገዳ በጊዜ ገደብ ተነስቷል

የዲስፕሊን ኮሚቴው የጅማ አባጅፋርን እገዳ በጊዜ ገደብ አንስቷል።

ከወር በፊት ጅማ አባጅፋሮች ከይስሃቅ መኩርያ እና ከሌሎች ተጫዋቾች ተያይዞ በተፈጠሩ ነገሮች በዲስፕሊን ኮሚቴ ከፌደሬሽኑ ማንኛውም አይነት ግልጋሎት እንዳያገኙ መታገዳቸው ይታወሳል።
አሁን ደግሞ ጅማ አባጅፋሮች ለኮሚቴው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት እገዳው በአንድ ወር ገደብ ተነስቷል።

እግዳው የተነሳበት ምክንያት የተባለው ደግሞ ጅማ አባጅፋሮች በቀጣይ ዓመት በውድድር ለመቆየት በቃል የተስሟሟቸው ተጫዋቾች የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት በፌዴሬሽኑ ማስፈረም እና ማስመዝገብ ስላለባቸው ቡድኑ እነዚህን ጉዳዮች እስኪያጠናቅቅ ከፌዴሬሽን ግልጋሎት እንዳያገኝ የተጣለበት ግልጋሎት በጊዜ ገደብ ተነስቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ