የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ እጣ ድልድል ወጥቷል

ከደቂቃዎች በፊት በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት የከንቲባው ተወካይን ጨምሮ የክለብ ተወካዮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የእጣ ማውጣቱ ስነስርዓት ተካሂዷል፡፡

በዚህም መሠረት

ምድብ ሀ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ባህርዳር ከተማ፣ ወልቂጤ፣ መከላከያ

ምድብ ለ፡ ኢትዮጵያ ቡና፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ወልዋሎ፣ ሰበታ ከተማ

በመክፈቻው ዕለት ቅዳሜ በ8 ሰዓት ባህር ዳር ከተማ ከወልቂጤ ከተማ የሚገናኙ ሲሆን በ10፡00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ ይጫወታሉ፡፡ ሰኞ ደግሞ በ8:00 ወልዋሎ ከኤሌክትሪክ፤ በ10:00 ኢትዮጵያ ቡና ከሰበታ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

በተያያዘም ለውድድር ጨዋታ መግቢያ የሚሆኑ ትኬቶች በኤሌክትሮኒክ የክፍያ ዘዴ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንና በተጨማሪም ለክለቦቹ የጨዋታዎቹን ቪዲዮዎች በግብአት መልኩ ለመስጠት ስለመታቀዱም ተነግሯል፡፡

በመርሃግብሩ ላይ በአዲስ አበባ እግርኳስ ፌደሬሽንና ውድድሩን በቀጥታ ሽፋን በሚሰጠው አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ መካከል የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ