ወልቂጤ ከተማ ጋናዊ ተከላካይ በማስፈረም ዝውውሩን ቋጭቷል

ክትፎዎቹ ጋናዊውን የመሀል ተከላካይ መሀመድ አወልን በማስፈረም የዝውውር መስኮት እንቅስቃሴያቸውን አጠናቀዋል፡፡

ጋና ከሚገኘው የፌይኖርድ አካዳሚ የተገኘው ቁመተ ረጅሙ ተከላካይ በበርካታ ሀገራት በመዟዟር የእግር ኳስ ህይወቱን አሳልፏል። በሁለት አጋጣሚዎች የተጫወተበት የሀገሩ ክለብ አሳንቲ ኮቶኮን ጨምሮ ለደቡብ አፍሪካው ማርቲዝበርግ፣ ለሞሮኮው ራጃ ካዛብላንካ እና አሴክ ሚሞሳ የተጫወተ ሲሆን በተጨማሪም ለሩሲያው አርሰናል ቱላ እንዲሁም ለኩዌቱ ክለብ አልፋ ሂል፣ ያለፉት ሁለት አመታት ደግሞ ለሳዑዲ አረቢያው አል-አንሳር ክለብ ተጫውቶ አሳልፏል።

ወልቂጤን በአንድ ዓመት ውል የተቀላቀለው መሐመድ የቶጎ ዜግነት ያላቸው ግብ ጠባቂው ሶሆሆ ሜንሳ እና አጥቂው ጃኮ አራፋትን በመከተል የክለቡ ሦስተኛ የውጪ ዜጋ ተጫዋች ሆኗል።


© ሶከር ኢትዮጵያ