ከፍተኛ ሊግ | ደደቢት ተከላካይ አስፈረመ

ከቀናት በፊት ከስሑል ሽረ ጋር በስምምነት የተለያየው የመሃል ተከላካዩ ዲሜጥሮስ ወልደሥላሴ ደደቢትን ተቀላቅሏል።

ባለፈው ዓመት መጀመርያ አዲስ አበባ ከተማ ለቆ ስሑል ሽረ በመቀላቀል ላለፈው አንድ ዓመት ቡድኑን በአምበልነት የመራው ይህ ተጫዋች በመሃል ተከላካይ ብዙ አማራጭ ለሌላቸው ደደቢቶች ጥሩ አማራጭ ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ቀደም በሐረር ቢራ፣ አዳማ ከተማ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ስሑል ሽረ የተጫወተው አንጋፋው ተከላካይ ለደደቢቶች የክረምቱ አስራ አንደኛ ፈራሚ ነው።

ወደ ፕሪምየር ሊጉ ዳግም ለመመለስ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም የሚገኙት ደደቢቶች በቀጣይ ቀናት የሁለት ተጫዋቾች ዝውውር ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ