ቢንያም በላይ የሚጫወትበት ስርያንስካ ወደ ታችኛው ሊግ ወረደ

በስዊድን ሱፐርታን (ሁለተኛ ሊግ) የሚወዳደረው እና ኢትዮጵያዊው አማካይ ቢንያም በላይ የሚጫወትበት የስዊድኑ ስርያንስካ ከአንድ ዓመት የሊጉ ቆይታ በኋላ ወደ ሦስተኛው የሃገሪቱ የሊግ እርከን መውረዱን አረጋግጧል።

በሊጉ የመጨረሻ ጨዋታዎች በሊጉ የመትረፍ ዕድሉ አስፍቶ የነበረው ይህ አንጋፋ ክለብ በዛሬው ዕለት በሜዳው በሃልምስታድስ ሁለት ለባዶ መሸነፉ ተከትሎ ነው ከሊጉ መውረዱ ያረጋገጠው። በውድድር ዓመቱ በአማካይነት እና በመስመር አጥቂነት ቡድኑን በቋሚነት ያገለገለው ቢንያም በላይ በዛሬው ጨዋታ ከዕረፍት በኃላ ተቀይሮ ወጥቷል።

በውድድር ዓመቱ መጀመርያ ስከንደርቡን ለቆ ከስዊድኑ ክለብ የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገው ቢንያም በላይ በቀጣይ ቀናት ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ