ከፍተኛ ሊግ | ሰሎዳ ዓድዋ አንድ ጋናዊን ጨምሮ ስድስት ተጫዋቾች አስፈረመ

በአንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ባስመዘገቡት ውጤት አምጥተው በዘንድሮ በከፍተኛ ሊግ መሳተፋቸው ያረጋገጡት ሶሎዳ ዓድዋዎች ስድስት ተጫዋቾች ሲያስፈርሙ የአስራ ሁለት ነባሮችን ውል አራዝመዋል።

ክለቡ ከተቀላቀሉት ተጫዋቾች መካከል ወልዋሎ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ የክለቡ አባል የነበሩት አማካዩ ኤፍሬም ኃይለማርያም እና ተከላካዩ መብራህቱ ኃይለስላሴ ይጠቀሳሉ።

ሌላው የክለቡ አዲስ ፈራሚ የቀድሞው የአሳንቲ ኮቶኮ እና ሳንጋ ባሌንዴ አጥቂ ጋናዊው ኢድሪስ ዓብዱል ናፉ ሲሆን ዓብዱሰላም ዮሴፍ (አጥቂ)፣ ዓብዱልጀሊል መሐመድ (ተከላካይ) እና ሚካኤል ፀጋይ (አማካይ) ክለቡን የተቀላቀሉ ሌሎች ተጫዋቾች ናቸው።

ክለቡ ከላይ ከተጠቀሱት አዳዲስ ተጫዋቾች በተጨማሪ የአስራ ሁለት ተጫዋቾችም ውል አራዝመዋል። አማኑኤል ዘርዑ፣ ፊልሞን ገ/እግዚአብሔር ፣ ተመስገን ገ/ህይወት፣ የማነ ገ/ሥላሴ፣ መሐሪ አድሐኖም፣ ሰለሞን በሪሁ፣ ተክሊት ፀጋይ፣ ሳምሶን በርኸ፣ ኃይልሽ ፀጋይ፣ የማነ ገ/ሥላሴ እና ቃልአብ ኪዱ ውላቸው በማራዘም ከክለቡ ጋር ለመቆየት ፊርማቸው ያኖሩ ተጫዋቾች ናቸው።


© ሶከር ኢትዮጵያ