14ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የመካሄዱ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል

በስምንት ቡድኖች መካከል ይካሄዳል ተብሎ የታሰበው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የመካሄዱ ነገር አጠራጣሪ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።

ውድድሩ የመካሄዱ ነገር አጠራጣሪ የሆነው ከወቅታዊ የሀገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ምክንያት እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ውድድሩን ለማካሄድ የሚያስችል ማረጋገጫ ከፀጥታ ኃላፊዎች ለማግኘት የአዲስ አባባ እግርኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ከሚመለከተው የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ሰምተናል። እስከ ነገ ድረስም የውድድሩ መካሄድ አለመካሄድ ማረጋገጫ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

14ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫን ከጥቅምት 22 – ኅዳር 7 ድረስ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለማድረግ የአአ እግርኳስ ፌዴሬሽን የተለያዩ ተግባራቶችን በማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ