የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ተራዘመ

በመጪው እሁድ ሊካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

በፕሪምየር ሊጉ አሸናፊ መቐለ 70 እንደርታ እና በኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊው ፋሲል ከነማ መካከል እሁድ ጥቅምት 23 በአዲስ አበባ ስታዲየም ሊደረግ መርሐ ግብክ ወጥቶለት የነበረው ይህ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ የመሸጋገሩ ምክንያት ምን እንደሆነ እና ቀጣይ እጣፈንታው በፌዴሬሽኑ አልተገለፀም። ሆኖም ከወቅታዊው የሀገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ አንፃር ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኃላፊነት መውሰድ አለመፈለጉ ምክንያት ስለመሆኑ እየተነገረ ይገኛል።

አዳዲስ ጉዳዮች እንደደረሱን ወደናንተ እናደርሳለን


© ሶከር ኢትዮጵያ